six month report (1)

Full text

(1)

በከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት የንብረት ግብር ሪፎርም አሃድ

  

2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት

የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ጥር/2014 አዲስ አበባ

(2)

ይዘት 1. መግቢያ

2. የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

3. ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰደ መፍትሄ

4. ወደፊት ትኩረት የሚፈልጉ ዋና ዋና ጉዳዮች

(3)

1. መግቢያ

• ከተሜነት እየተስፋፋ በመሄድ ላይ መሆኑ

• የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ጥያቄወች ፍላጎት መጨመሩ

• የከተሞችን የገቢ አሰባሰብ በማዘመን እና ገቢያቸው እንዲሻሻል ማድረግ

• ዘመናዊ የንብረት ግብር ሲስተም የማልማት ስራ ወደ ተግባር የማስገባት፣

(4)

• የእርግጥ ንብረት ግመታ ስራዎችን ማከናወን

• የመሬት ይዞታ ማህደር አያያዝ ማዘመን

• የተለያዩ ጥናቶችን ማዘጋጀት

• ሀገራዊ አዋጆችን እና ደንቦችን ማዘጋጀት

• በ2014 በጀት ዓመትም የተለያዩ ግቦችና ተግባራትን በማቀድ ወደ ስራ የገባ ሲሆን

• የግማሽ አመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደተመለከተው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

(5)

2. የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ግብ 1 ፡ የፌደራል የንብረት ግብር አዋጅ፤ ሞዴል የክልል ንብረት ግብር ደንብ እንዲሁም ሞዴል መመሪያና ጋይድላይን ሰነዶች እንዲሟሉ እና እንዲጸድቁ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፡፡

የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት

• የንብረት ግብር አዋጅ ለተወዮች ም/ቤት የሚላከው በገንዘብ ሚ/ ር በኩል በመሆኑ ክትትል የማድረግ ስራ እየተሰራ ሲሆን አፈጻጸም 100% ነው፡፡

• ሞዴል የክልል ንብረት ግብር ደንብ እና መመሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ ሞዴል ደንብ የተዘጋጀ ሲሆን መመሪያ ለማዘጋጀት ፐሮፖዛል ተዘጋጅቷል፡፡ አፈጻጸም 80 % ነው፡፡

(6)

ግብ 2 ፡የፌደራል የሪል ሰቴት ልማት፣ ግብይትና ግመታ አዋጅ ፤ ክልላዊ ሞዴል ደንብ እንዲሁም መመሪያና ጋይድላይን ሰነዶች እንዲሟሉ እና እንዲጸድቁ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፡፡

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• ከቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ከህግ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን በማስተካከል ለከተማና መሰረተ ልማት ሚ/ ር እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

በፐ/ጽ/ቤቱ ከተሰጠው ተልኮ እንጻር አፈጻጸሙ 100% ነው፡፡

• የክልሎች ሞዴል ደንብ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ወቅታዊ የማድረግ ስራ ተከናውኗል፡፡ አፈጻጸም 100% ነው፡፡

• በተዘጋጀው ሞዴል ደንብ ላይ ውይይት ለማድረግ ፐሮፖዛል ተዘጋጅቷል፡፡

አፈጻጸም 80% ነው፡፡

(7)

ግብ 3 ፡ የፌደራል እና የክልል ሞዴል የከተማ መሬት ነባር ይዞታ ኪራይ አስተዳደር ደንብ ይዘጋጃል፣

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• በበጀት ዓመቱ አንድ የከተማ መሬት ነባር ይዞታ ኪራይ ደንብ ተዘጋጅቷል፡፡

• በተዘጋጀው ሞዴል ደንብ ላይ የመሬት ዘርፍ ባለሙያዎች፣ የገቢዎች ባለሙያዎች እና የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንዲሳተፉ በማድረግ ውይይት በማድረግ መረጃ የማሰባሰብ ተግባር ተፈጽሟል፡፡ የሁለቱም ተግባራት አፈጻጸም 100% ነው፡፡

(8)

ግብ 4 ፡ በፊደራል፤ በ5 ክልሎችና በ 6 ከተሞች የንብረት ግብይትና ግመታ ባለሙያዎች ፈቃድ አሰጣጥ ስርአት እንዲዘረጋ ይደረጋል፡፡

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• የንብረት ግብይት እና ግመታ ባለሙያዎች እና አገበያዮች የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል መስፈርት በውስጥ ባለሙያዎች ወቅታዊ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

• የንብረት ግብይት እና ግመታ ባለሙያዎች እና አገባባዮች የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ወቅታዊ የማድረግ ስራ የተሰራ ሲሆን ወደፊት በሚዘጋጁት መድረኮች ባለድርሻ አካላትን በማሰተፍ አስተያየት እንዲሰጥበት በማድረግ እንዲዳብር ይደረጋል፡፡ የሁለቱም ተግባራት አፈጻጸም 100% ነው፡፡

• ከተሞች የንብረት ግብይትና ግመታ ባለሙያዎች ፈቃድ አሰጣጥ ስርአት መመሪያ የተዘጋጀ ቢሆኑም የግብይትና ግመታ አዋጁ ባለመጽደቁ ምክንያት ወደ ክልል ባለመውዱ ክትትል አልተደረገም፡፡ አፈጻጸሙ 83% ነው፡፡

(9)

ግብ 5 ፡ በ18 ከተሞች 630000 የሚሆን የይዞታ ፋይል በዘመናዊነት እንዲደራጅ ይደረጋል

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• ለፋይል ማደራጀት የነባራዊ ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ለመገምገም የፌደራል ፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የቴክኒክ ኮሚቴ እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ወርክ ሾፕ በማዘጋጀት የጥናቱን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል፡፡ አፈጻጸም 100% ነው፡፡

• በአማካሪ ድርጅቱ የተዘጋጀወን ለከተሞች የሚያስፈልግ የHardware ግዥ ቢጋር በመገምገም ግብረ-መልስ ተሰጥቷል፡፡ አፈጻጸም 100%

ነው፡፡

• አማካሪ ድርጅቱ ፋይል ማደራጀት ስራ በወሩ በተያዘው አቅድ መሰረት በ12 ከተሞች 131229 ፋይል የማደራጀት ስራ የተሰራ ሲሆን አፈጻጸም 21% ነው፡፡

(10)

• ስራው በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ መሰረት መፈጸም ባለመቻሉ ምክነያት የመሬት ይዞታ ማህደር ስካን የማድረግ ስራ እስካሁን አልተጀመረም፡፡

• የፋይል ምዝገባ ስራውን የሚሰራውን ድርጅት ድጋፍ ክትትል ማድረግ በሚመለከት

• ከመስክ ክትትልና ድጋፍ ከተደረገ በኋላ ለከተሞች እና ለአማካሪ ድርጅቱ የጽሁፍ ግብረ መልስ በመስጠት ያለውን ለውጥ ለመከታተል ክልሎችን በመከፋፈል በስልክ ክትትልና ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የተገኙ መረጃዎች መሰረት በማድረግ በተመረጡ ከተማ አስተዳደሮች ለአማካሪ ድርጅቱ የተሰጠውን ግብረ መልስ መነሻ በማድረግ ውሳኔ ለመስጠት እውነታውን ለማረጋገጥ በተመረጡ ከተሞች(አዳማ፣

ቢሸፍቱ፣ ሻሸመኒ እና ጅማ) መረጃዎች የማሰባሰብ ስራ ተከናውኗል፡፡

(11)

• በተሰበሰበው መረጃ መሰረት በማድረግ የፕ/ጽ/ቤት ኃላፊ እና

የከተሞች ገቢ ማሻሻያ ፣ ፈንድ ሞብላይዜሽንና ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በአካል በመገኜት ችግሮች በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

• አማካሪ ድርጅቱን በተመለከተ በመጀመሪያ ኃላፊዎች ወደ ዉጭ ወጥተው ስለነበር በዙም ስብሰባ በማድረግ በችግሮች ላይ ውይይት በማድረግ ሃገር ውስጥ መጥተው መወያየት እንደሚያስፈልግ ስምምነት ላይ በመደረሱ በአካል ችግሮች በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ቀሪ ስራዎችን በፍጥነት በሚከናወኑበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ አፈጻጸም 100% ነው፡፡

(12)

City Files Organised No of parcels

verified in the field Comment

Adama 2,703 20,175

Bishoftu 6,796 1,717

Shashamane 9,399 9,090

Jimma 21,577 2,770

Nekemte - 0 Not yet started

Debre Birhan 3,728 0

Diredawa 24,710 270

Harar 19,977 0

Jigjiga - 0 Yet to start, Completed Situation Assessment

Bahir Dar 19,491 0

Gondar 15,208 3,124

Debre Markos - 0 Yet to start, Completed Situation Assessment

Dessie - 0 Activities suspended

Dilla 643 2,375 Field data collection is ongoing. File re-organisation to start soon

Hawasa - 2,669

Sodo 1,554 1,803 Field data collection is ongoing. File re-organisation to start soon

Arbaminch 5,443 2,715 Field data collection is ongoing. File re-organisation to start soon

Hosana - 0 Yet to start, Completed Situation Assessment

TOTAL 131,229 46,708

Appendix 4: Summary of File organized per city

(13)

ግብ 6 ፡በ2 ክልልና በ2 ከተሞች የንብረት ግብር መረጃ ስርዓት /Bussine process Part/ ከለማው ሲስተም ጋር እንዴት እንደሚሰራበት የስራ ላይ ስልጠና በማመቻቸትና በተቀናጀ መልኩ ለ 50 ሰልጣኞች ስልጠና እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• በሁለት ከተሞች ማለትም በድሬዳዋ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ በለማው የንብረት ግብር ሲስተም አጠቃቀም ሲሆን በመጀመሪያ ለሚሰጠው የድሬዳዋ የስራ ላይ ድጋፍ እና ስልጠና መስጠት የሚያስችል ፐሮፖዛል ተዘጋጅቷል፡፡

• በግማሽ አመቱ 20 ባለሙያዎች ለማሰልጠን ታቅዶ ለ29 (24 ወንድ እና 5 ሴት) ሰልጣኞች ስልጠናው ተሰቷል፡፡

• የተሰጠው ስልጠና ውጤታማነት ለመገምገም የሚያስችል መጠይቅ ተዘጋጅቷል፡፡ የሁሉም ተግባራ አፈጻጸም 100% ነው፡፡

(14)

ግብ 7 የለማውን የንብረት ግብር ሲስተም በመረጃ ወቅታዊ ለማድረግ የ 3 ከተሞችን የግንባታ ነጠላ ዋጋ የሚያሳይ ሰነድ በማዘጋጀት የ2014ዓ/ ም ወቅታዊ ይደረጋል፡፡

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• ከተሞች ያወጡትን የግንባታ እቃዎች መረጃ ማሰባሰቢያ ቅፅ ተዘጋጅቷል፡፡

• የለማውን የንብረት ግብር ሲስተም በመረጃ ወቅታዊ ለማድረግ የ 2 ከተሞችን የግንባታ ነጠላ ዋጋ የሚያሳይ ሰነድ በማዘጋጀት የ2014ዓ/ ም ወቅታዊ የሆነ የትንተና ስራ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

• በተዘጋጀው ወቅታዊ መረጃ መሰረት የነጠላ ዋጋና የግንባታ ዕቃ በሜትር ካሬ መሰረት አዲሱን ዋጋ የማውጣት ስራ ተከናውኗል፡፡

የሁሉም ተግባራት አፈጻጸም 100% ነው፡፡

(15)

ግብ 9፡- በድሬድዋ ከተማና በባህር ዳር ከተማ የተጀመረዉ 4000 ልዩ ባህሪይ ያላቸው ንብረቶች መረጃ ለቀማና ዋጋ ግመታ ስራ ጥናት እንዲጠናቀቅ ይደረጋል፡፡

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• በአማካሪ ድርጅቱ የተዘጋጁ ሰነዶች ማለትም የአቅም ግንባታ የፍልጎት ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት፣ የስልጠና ማኑዋል እና የልዩ ባህሪ ያላቸው ንብረቶች ግመታ ሪፖርት ተዘጋጅተው የቀረቡ ሲሆን የማጠቃለያ ወርክ ሾፕ በማዘጋጀት የስራውን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራ ተከናውኗል፡፡

በአጠቃላይ የዋጋ ግመታ የተከናወነባቸው ልዩ ባህሪ ያላቸው ንብረቶች ብዛት 2862 ሲሆን ይህም በእቅዱ ከተያዘው 4000 ንብረት መገኘት የቻሉትን ንብረቶች 100% ተሰርቶ ጥናቱ ተጠናቋል፡፡

• የመጨረሻ ሰነዶችን በቴክኒክ ኮሚቴ እና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ወርክ ሾፕ ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ርክክብ ተፈጽሟል፡፡ አፈጻጸም 100%

ነው፡፡

•  

(16)

• በሶስተኛ ምዕራፍ ከጥናቱ የሚጠበቁ ውጤቶች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ማኑዋሎች እና የጥናት ሰነዶች በከተሞች እና በፌደራል የጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች አስተያየት እየተሰጠበት እንዲሁም ባላድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ በወርክ ሾፕ አስተያየት ተሰጥቶባቸው የቀረቡ ሲሆን እንዚህም የሚከተሉት ናቸው

• Institutional capacity building and training need assessment study

• Training and guideline manual

• Valuation report

• Implementation strategy and recommendation ፡፡

ሲሆኑ አፈጻጸም 100% ነው፡፡

(17)

ግብ 10 ፡ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ስር ከሚገኙ ክፍሎች ጋር በEoI, TOR, RFP ዝግጅት እና የቴክኒክ ግምገማዎች ላይ በቅንጅት ይሰራል፡፡

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

• በተለያዩ የቴክኒክ ኮሚቴ አባል በመሆን የሰነድ ግምገማ ማድረግ ስራ ተከናውኗል ከዚህ ውስጥ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጃት መዋቅር ሰነድ ዝግጅት፣ የጨረታ ሰነድ መገምገም እና የህግ ማዕቀፍ ወቅታዊ ማድረግ ስራዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

• የአቅም ግንባታ በሚያዘጋጀው የስልጠና ፕሮግራሞች የእርግጥ ንብረት ግመታ የሙያ ደረጃ ዝግጅት በማደረግ እና በህግ ማዕቀፎች ላይ ስልጠና በመስጠት ተሳትፎ ተደርጓል፡፡ የሁለቱም ተግባራት አፈጻጸም 100%

ነው፡

(18)

3. ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሄዎች

ያጋጠሙ ችግሮች

• የከተማ መሬት ይዞታ ማህደር ማደራጀት ስራ ውል ወስዶ በመስራት ላይ ያለው አማካሪ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን እና ተግባሮችን በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ ማጠናቀቅ ያለመቻል

• ከተሞች ለከተማ መሬት ይዞታ ማህደር ማደራጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ማቅረብ ያለመቻል

• የተዘጋጁ የሪል ስቴት ንብረት ግብይት እና ግመታ አዋጅ፣ የንብረት ግብር አዋጅ እና የፋናንስ ስትራቴጂ በሚመለከታቸው አካላት ባለመጽደቃቸው ምክንያት ቀጣይ ስራዎችን ማከናወን አለመቻሉ፣

(19)

የተወሰዱ መፍትሄዎች

• በከተሞች በመገኜት በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ለአማካሪ ድርጅቱ ግብረ መልስ መስጠት እና በዙም እና በአካል በተደረገ ስብሰባ ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት ተደርጓል

• ከተሞች ማቅረብ የሚገባቸውን ግብዓት በተመለከተ አመራሮች በተገኙበት የተለያዩ የበጀት ምንጮችን ተጠቅመው በአስቸኳይ እንዲያማሉ ድጋፍ ተደርጓል

• የተዘጋጁ ህጎች በሚመለከታቸው አካላት እንዲፀድቁ ክትትል ማድረግ እና ለሚመለከታቸው አካላት በተደጋጋሚ የማሳሰብ ስራ እየተሰራ ነው

፡፡

(20)

4. ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

• በ18 ከተሞች የሚተገበረው የመሬት ይዞታ ማህደር ማደራጀት እና ሲስተም ልማት ስራ

(21)

እናመሰግናለን !

Figure

Updating...

References

Updating...

Related subjects :